የላጋር የንግድ ማዕከል እና መኖሪያ ቤት ሁለት
የላጋር የንግድ ማዕከል እና መኖሪያ ቤት ቅንጡ አፓርታማዎች ምቾትና ጥራትን ለነዋሪዎች ለመስጠት ትኩረት አድርገው የተገነቡ ናቸው፡፡ ሁሉም መኖሪያ ቤቶች እዚህ መኖር በሕልም ውስጥ የመኖር ያህል እንዲሰማዎ የሚያደርጉ ልዩ ባህሪያትን ይዘዋል፡፡
ዘመኑን ያማከለ የንግድ ማዕከል እና መኖሪያ ቤት
በከተማችን እምብርት የሚገኘው የላጋር የንግድ ማዕከል እና መኖሪያ ቤት ለነዋሪዎች እና ሸማቾች ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ ህንጻው የተለያዩ የቅንጦት መገልገያዎችን፣ ዘመናዊ መደብሮችን እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሬስቶራንቶችን ምቹ በሆነ እና ስነውበትን በተላበሰ ህንጻ ውስጥ ይዞ ቀርቧል፡፡
ዘመኑን ያማከለ የንግድ መዳረሻ
የላጋር ልዩ የንግድ መዳረሻ ወደር የለሽ ጥራት ያላቸውን እቃዎች ለመገበያየት የሚያስችል ነው፡፡ ማዕከሉ የተለያዩ የቤት ውስጥ እና የውጪ የምግብ እና የመጠጥ አማራጮችን እንዲሁም ለሁሉም ተስማሚ የሆነ ዘመናዊ የህንጻ አወቃቀር አለው፡፡
የንግድ ማዕከል
ላጋር ለከተማይቱ አዲስ የሆነ የንግድ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ቅንጡ አፓርትመንቶች፣ የገበያ ማዕከላት፣ የምግብ እና የመጠጥ መሸጫ ቦታዎች፣ አረንጓዴ ፓርኮች እና በቅርብ የሚገኙ ባለ 5 እና ባለ 4 ኮከብ ሆቴሎችን የሚያካትት ነው።